GAMBY Library

ዊሊያም ሼክስፒር

“ሲዖል ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት እዚህ ምድር ላይ ነው፡፡”
.
☞ “ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ ቅንና መልካም ስትሆን ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።”
.
☞ “ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ፤ ሁሉንም ውደድ፤ ጥቂቶቹን እመን፤ ማንንም ግን አትበድል፡፡”
.
☞ “የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።”
.
☞ “ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አይችልም።”
.
☞ “የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።”
.
☞ “መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ቀንዲል ናት።”
.
☞ “ማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው።”

የቀድሞው የዝምባብዊ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በተለያዬ ወቅት የተናገሯቸው አስቂኝና አዝናኝ አባባሎች እንሆ ተጋበዙልኝ።

1. “ኦባማ በሃገሬ ዚምባብዌ ላይ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መፈቀድ አለበት የሚለኝ ከሆነ መጀመሪያ እኔ እርሱን ማግባት አለብኝ ኦባማን የማገባው ለማሳያነት ነው!”
2. “አፍሪካ ውስጥ በስነ-ስርዓት የሚከበረው ማስጠንቀቂያ “battery low !”የሚለው ብቻ ነው!”
3. “ችግርህን ለመናገር ሐይማኖት ቦታ ትሄዳለህ፣ ደስታህን ለመግለፅ ጭፈራ ቤት ትገባለህ፣ ለዚህ ነውኮ ገነት ወይም ጀነት ለመግባት እድልህ የጠበበው!”
4. “አውሮፓውያን ወደ አውሮፓ እንዳንገባ በኛ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል፡፡ ሆኖም የጣሉት ማዕቀብ እኛን አይጎዳም፡፡ ለምን ቢባል እኛ ሲጀመር አውሮፓውያን አይደለንማ!”
5. “ሴቶች በሙሉ የኤድስ መድሃኒት እስኪገኝ ድረስ የግብረ ስጋ ግንኙነት (Sex) አንፈጽምም ብለው ቢያምጹ ኖሮ ወንዶች በ30 ቀናት ውስጥ መድሃኒቱን ባገኙት ነበር!”
6. “99% የዳይመንድ ምርት የሚገኘው አፍሪካ ውስጥ ቢሆንም አፍሪካውያን ግን የሚያብለጨልጩት በቫዝሊን ነው!”
7. “ትዳር እያለህ ከተማሪ ሴቶች ጋር መውጣት ደስ የሚልህ ከሆነ ለሚስትህ የተማሪ ዩኒፎርም ግዛላት!”
8. “ወደ ኬንያና ናይጄሪያ ስትሄዱ ኪሳችሁን ጠብቁ!”
9. “ናይጄርያን የመሰሉ ብዙ ቋንቋዎች የሚናገር ህዝብ ያላቸው አገሮች ዱዳ (መስማት የተሳነው) ፕሬዝደንት ነው የሚያስፈልጋቸው!”
10. “ክርስቶስ አንድ ጊዜ ሙቶ አንድ ጊዜ አረገ፣ እኔ ግን ብዙ ጊዜ ሙቻለሁ። ያኔ ነው ክርስቶስን ያሸነፍሁት!”
11. “ኔልሰን ማንዴላ ለነጮቹ ያሳያቸው እንክብካቤ ወደ ቅድስና የሚቀራረብ ነው፡፡ በመሆኑም ከአሁን በኋላ የቅድስና ማዕረግ ተሰጥቶት “ቅዱስ ማንዴላ” መባል አለበት!
12. “አዳምና ሄዋን ቻይናዊያን ቢሆኑ ኖሮ እስካሁን ድረስ ገነት ውስጥ በኖርን ነበር። ምክንያቱም የእጸ በለስ ፍሬውን ትተው እባቡን በበሉት ነበር!”
13. “ነጮች አፍሪካ ውስጥ መጥተው የአፍሪካዊያን አሰሪ ይሆናሉ፡፡ አፍሪካዊያን ደግሞ አውሮፓ ሄደውም የነጮች ሰራተኛ ነው የሚሆኑ!”
14. “ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ሰዎች እርስበርስ እንዲጋቡ ልንፈቅድ እንችላለን፡፡ ነገር ግን በአንድ ጉዳይ ላይ መስማማት አለብን። ግብረሶዶማውያኑ በአምስት አመታት የትዳር ቆይታቸው ልጅ ወልደው እንዲያሳዩን ቃል ይግቡልን፡፡ በሰጠነው ጊዜ ገደብ ልጅ ወልደው የማያሳዩን ከሆነ ግን በስምምነታችን መሠረት አንገታቸውን ቀልተን እንጥለዋለን!”
15. “ከአንድ ሰው በላይ የምታፈቅር ከሆነ ውስጥህ ያለው ልብ ሳይሆን ‘memory card’ ነው!”
16. “በግሩፕ ነጮች ወደ አፍሪካ ከመጡ ቱሪስት ይባላሉ፡፡ በብዛት አፍሪካዊያን ወደ አውሮፓ ከሄዱ ደግሞ ረፍዩጂስ (ስደተኞች) ይባለሉ!”
17. “ነጭ ሰው ሊታመን የሚችለው የሞተ ከሆነ ብቻ ነው!”
18. “የውጭ ሀገር ዜግነት ያላትን ሴት የመሳም ዕድል ካጋጠመህ በደምብ ግጥም አድርገህ ሳማት፡፡ ሴትዮዋን እየሳምካት ያለኸው መላውን የዚምባብዌ ሕዝብ ወክለህ መሆንህን አትርሳ!”
19. “አንዳንድ ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለህ ስትመለከት ከእናትህ በላይ ለሴት ልጅ ገንዘብ የምታጠፋ ከሆነ ያኔ እጀ-ሰብ እውነት መሆኑ ይገባሃል!”
20. “ሴቶች እህቶቼ አንድ ነገር ልምከራችሁ፡፡ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ብቻ እያስታወሰ “ውዴ ናፍቀሽኛል!” የሚል አጭር የጽሑፍ መልእክት የሚልክላችሁን ወንድ አትመኑት እናተ ጃንጥላ አይደላችሁምና”
21. “አንድ መቶ በሚያክሉ የሰርግ ስነስርዓቶች ላይ ተገኝተህ ስታበቃ አንድ ለፍቅር የምትሆንህን ሴት ካጣህ በቃ አንተ አጎበር ነህ!”
22. “አንዳንድ ሴቶችን ስትመለከት ጂም የሚሰሩ ይመስላሉ። ግን የጂምናዝየምን በር እንኳ አይተውት አያውቁም። ሆኖም ግን ከአንዱ ወንድ ወደ ሌላው ወንድ ለመሮጥ ሲሉ ቅርጻቸውን ይጠብቃሉ!”
23. ሌላ እንተወውና ሴጣን እንኳ ግብረሰዶማዊ አልነበረም፡፡ ያኔ ራቁቷ የነበረችውን ሔዋንን ነበር የፈተነው! ራቁቱ የነበረውን አዳምን አይደለም!”
24. “ሰይጣን ራሱ gay አልነበረም! ምክንያቱም እራቁቱን ከነበረው አዳም እራቁቷን የነበረችውን ሄዋንን ስለመረጠ!”
25. “ዓለም አፍሪካን በድላታለች ከአውሮፓ አንድ ነጭ ወደ አፍሪካ ከመጣ የውጪ ዜጋ ጎብኚ ይባላል። ከአፍሪካ አንድ አፍሪካዊ ወደ አውሮፓ ከሄደ ግን ህገ ወጥ ስደተኛ ይባላል፡፡
26 “አምላክ ምርጥ ተመራማሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከወንድ ልጅ የጎድን አጥንት ወስዶ ድምጽ ማጉያ (loud speaker) ፈጠረ!”
27. “የጋና ሴቶች ፍቅር የሚይዛቸው የATM ማሽን ያለበት አካባቢ ላይ ነው!”
28. አስቀያሚ ከሆንክ አስቀያሚ ነህ ስለ ውስጣዊ ውበት አትናገር ምክንያቱም X-ray እያየን አይደለም የምንሄደው!”
29. “ገንዘብ ፍቅርና ጤና አይገዛም ይላሉ እኔም እስማማለሁ ነገር ግን እስኪ ንገሩኝ ድህነት ምን ይገዛል?!”
30. “ንጉሳዊ ስርአቱ ሳይከፋፍላት አፍሪካ ወደ ነበረችበት መመለስ አለባት። እነዚህ ሰው ሰራሽ መከፋፍሎች ናቸው። ባለን አፍሪካዊ ስሜት እናስወግደዋለን!”